በርካታ-ማስነሻ

ሁል ጊዜ Windows በ መጀመሪያ ይግጠሙ

እርስዎ በሚገጥሙበት ጊዜ Windows ሌሎች የ መስሪያ ስርአቶችን ፈልጎ አያገኝም እና የ ማስነሻ ዝርዝር አይፈጥርም: በ እርስዎ የ ማስነሻ ዝርዝር ላይ ደርቦ ይጽፍበታል: እና የ እርስዎ ኮምፒዩተር በ ቀጥታ Windows ያስነሳል

ሊነክስ ሚንት (እና በርካታ የ ሊነክስ መስሪያ ስርአት) ሌሎች የ መስሪያ ስርአቶችን መለየት ይችላሉ እና ዝርዝር ይገነባሉ: እርስዎ የሚመርጡበት የትኛውን ስርአት እንደሚያስጀምሩ

እርስዎ ድርብ-ማስነሻ ወይንም በርካታ-ማስነሻ ከ Windows ጋር መፍጠር ከ ፈለጉ: ቀላሉ መንገድ እና እኛ የምንመክረው በ መጀመሪያ Windows እንዲገጥሙ ነው: ሊነክስ ሚንትን ከ መግጠምዎት በፊት

የ ማስነሻ ቅደም ተከተል መጠገኛ

በ እርስዎ የ ማስነሻ ቅደም ተከተል ላይ Windows ደርቦ ከ ጻፈበት

  1. ሊነክስ ሚንት ማስነሻ በ live ዘዴ (በ እርስዎ USB stick ወይንም ዲቪዲ).
  2. ተርሚናል ይክፈቱ
  3. የ እርስዎን ክፍልፋይ ዝርዝር ለ መመልከት: ይጻፉ lsblk -f.
_images/lsblkf.png

ሊነክስ ሚንት የ ተገጠመበትን ክፍልፋይ ፈልገው ያግኙ: በ በርካታ ስርአቶች ውስጥ የሚሆነው በ ext4 ክፍልፋይ ውስጥ ብቻ ነው

በ መመልከቻ ፎቶ ከ ላይ በኩል:

  • sdb የ USB stick ነው (የሚታወቀው በ iso9660 ይጻፉ የሚመሳሰለውን ወደ ISO image).
  • sda ሀርድ ድራይቭ ነው
  • sda4 ክፍልፋይ ነው በ sda ሀርድ ድራይቭ ውስጥ: ሊነክስ ሚንት የ ተገጠመበት

የ ክፍልፋይ ዝርዝር መጠን ለ መመልከት: ይጻፉ lsblk:

_images/lsblk.png

የ ክፍልፋይ ዝርዝር ምልክት ለ መመልከት: ይጻፉ blkid:

_images/blkid.png
  1. የ ሊነክስ ሚንትን ክፍልፋይ ይጫኑ እና የ grub ዝርዝርን እንደገና ይግጠሙ በሚቀጠልው ትእዛዝ መሰረት:
sudo mount /dev/sda4 /mnt
sudo grub-install --root-directory=/mnt /dev/sda

Warning

ከ ላይ እንዳለው ትእዛዝ ይቀይሩ /dev/sda4 and /dev/sda በ ተገቢው ስም ለ ሊነክስ ሚንት ክፍልፋይ እና የ እርስዎ ሀርድ ዲስክ አካል መሰረት