ሊነክስ ሚንት ማስነሻ

እርስዎ አሁን ሊነክስ ሚንት በ USB stick (ወይንም ዲቪዲ) አለዎት: ኮምፒዩተሩን ያስነሱ

  1. ያስገቡ የ እርስዎን USB stick (ወይንም ዲቪዲ) ወደ ኮምፒዩተር ውስጥ

  2. ኮምፒዩተሩን እንደገና ያስጀምሩ

  3. የ እርስዎ ኮምፒዩተር የ ነበረውን የ መስሪያ ስርአት ከ መጫኑ በፊት (Windows, Mac, Linux) አንዱን ለ እርስዎ መታየት አለበት ይህ BIOS loading screen. የ እርስዎን ኮምፒዩተር መመልከቻ ሰነድ ይመርምሩ የትኛውን ቁልፍ ሲጫኑ የ እርስዎን ኮምፒዩተር ማስነሻ እንደሚቀየር ወደ USB (ወይንም ዲቪዲ) ማስጀመሪያ

Note

በርካታ BIOS የ ተለየ ቁልፍ አላቸው: እርስዎ የሚጫኑት የ ማስነሻ አካል ለ መምረጥ: እና ሁሉም የ ተለየ መግቢያ ቁልፍ አላቸው ወደ BIOS ማሰናጃ መመልከቻ ለ መግባት (እርስዎ የ ማስነሻ ቅደም ተከተል የሚመርጡበት): ይህ ሁኔታ እንደ የ BIOS, አይነት ይለያያል: እነዚህ የ ተለዩ ቁልፎች መሆን ይችላሉ እንደ Escape, F1, F2, F8, F10, F11, F12 ወይንም Delete. ይህ መረጃ አብዛኛውን ጊዜ ኮምፒዩተሩ በሚነሳበት ጊዜ በ መመልከቻው ላይ ይታያል:

Hint

በ Macs, ተጭነው ይያዙ Alt ወይንም Option ቁልፍ የ ማስጀመሪያ ድምፅ ከ ሰሙ በኋላ

  1. የ ሊነክስ ሚንት ISO በ ሁለቱም መንገድ ማስጀመር ይቻላል በ EFI ወይንም BIOS ዘዴ: በ EFI ዘዴ ይህን የ grub ዝርዝር ያሳያል: በ BIOS ዘዴ የ isolinux ዝርዝር ያሳያል.

_images/isolinux.png

የ isolinux ዝርዝር በ BIOS ዘዴ ውስጥ

_images/grub-efi.png

የ grub ዝርዝር በ EFI ዘዴ ውስጥ

  1. ከ እነዚህ ዝርዝር አንዱን ይጫኑ Enter ሊነክስ ሚንትን ለ ማስጀመረ ከ እርስዎ USB stick (ወይንም ዲቪዲ) ውስጥ