ሊነክስ ሚንት በ ቅድሚያ-መግጠሚያ (በ OEM አገጣጠም)
በ ISO ማስነሻ ዝርዝር ውስጥ: OEM መግጠሚያ
ሊነክስ ሚንት በ ቅድሚያ ለ መግጠም ነው
ይህ ምርጫ በጣም ጠቃሚ ነው:
ሊነክስ ሚንትን ገጥመው ለ ደንበኞቻቸው መሸጥ ለሚፈልጉ አምራቾች እና ሻጮች
ሰዎች ኮምፒዩተሩን ለ ሌላ ሰው መስጠት ወይንም መሸጥ ለሚፈልጉ
እርስዎ ሊነክስ ሚንትን በ OEM
ዘዴ ሲገጥሙ: የ መስሪያ ስርአቱ የሚገጠመው በ ጊዚያዊ ተጠቃሚ መግለጫ ነው: እና ኮምፒዩተሩ ለ ወደፊቱ ባለቤት ይሰናዳል
የ ተጠቃሚ መግለጫ የሚሰናዳው በ አዲሱ የ ኮምፒዩተር ባለቤት ነው
የ OEM አገጣጠም ለ መፈጸም የሚቀጥለውን ደረጃ ይከተሉ:
ይምረጡ የ
OEM መግጠሚያ
ከ USB stick (ወይንም ዲቪዲ) ዝርዝር ውስጥመግጠሚያውን ያስጀምሩ እና የ መግጠሚያውን ትእዛዝ ይከተሉ:
ኮምፒዩተሩን እንደገና ያስጀምሩ
እርስዎ ከ ፈለጉ የ ስርአቱን ማሰናጃ መቀየር ወይንም ተጨማሪ ሶፍትዌር መግጠም ይችላሉ
ዝግጁ ሲሆኑ ይጫኑ ለ መጨረሻ ተጠቃሚ ለ መላክ በ ዝግጅት ላይ: እርስዎ የሚመርጡትን የ መግቢያ ቃል ያስገቡ በሚገጠም ጊዜ: ይጫኑ እሺ እና ኮምፒዩተሩን ያጥፉ
አዲሱ የ ኮምፒዩተር ባለቤት ኮምፒዩተሩን በሚያስጀምር ጊዜ የሚቀጥለው መመልከቻ ይታያል:
አዲሱ የ ኮምፒዩተር ባለቤት የ ተጠቃሚ ስም: የ መግቢያ ቃል: የ ፊደል ገበታ እቅድ: ቋንቋ: የ ሰአት ክልል: እና የ ራሳቸውን መግለጫ መፍጠር ይችላሉ