ሊነክስ ሚንት መግጠሚያ

በ ቀጥታ ክፍል ጊዜ

እርስዎ ከ USB stick በሚያስነሱ ጊዜ (ወይንም ዲቪዲ): ሊነክስ ሚንት የሚጀምረው በ ቀጥታ ክፍለ ጊዜ ነው: እርስዎን ራሱ በራሱ በ ቀጥታ የሚያስገባው ወደ ተጠቃሚ ሊነክስ ሚንት ነው እና እርስዎን የሚያሳየው ዴስክቶፕ ከ መግጠሚያ ጋር ነው:

_images/cinnamon.png

የ ሊነክስ ሚንት በ ቀጥታ ክፍለ ጊዜ

ይህ ቀጥታ ክፍለ ጊዜ ከ መደበኛ ክፍለ ጊዜ ጋር ተመሳሳይ ነው (ይህም ማለት: ሊነክስ ሚንት አንድ ጊዜ በ ቋሚነት በ ኮምፒዩተሩ ላይ እንደ ተገጠመ): ነገር ግን ከሚቀጥለው በስተቀር:

 • የ ቀጥታ ክፍለ ጊዜ ዝግተኛ ነው (የሚጫነው ከ USB stick ወይንም ዲቪዲ ነው: ሲወዳደር ከ SSD ወይንም HDD) ጋር
 • በ ቀጥታ ክፍለ ጊዜ ውስጥ እርስዎ የ ፈጸሙት ለውጥ ቋሚ አይደለም: እና ወደ USB stick (ወይንም ዲቪዲ) ውስጥ አይጻፉም: እና በ መግጠሚያው ላይ ምንም ተፅእኖ አይፈጥርም
 • አንዳንድ መተግበሪያዎች የሚሰሩት በ ተለየ መንገድ ነው (ወይንም አይሰሩም) በ ቀጥታ ክፍለ ጊዜ ውስጥ (Timeshift, Flatpak, የ ማሻሻያ አስተዳዳሪ: እንኳን ደህና መጡ መመልከቻ..ወዘተ)

Hint

የ ተጠቃሚ ስም ለ ቀጥታ ክፍለ ጊዜ mint ነው: የ መግቢያ ቃል ከ ተጠየቁ ይጫኑ Enter

ሊነክስ ሚንት በ ኮምፒዩተር ላይ መግጠሚያ

እርስዎ በ ቋሚነት ሊነክስ ሚንትን በ ኮምፒዩተሩ ላይ ለ መግጠም

 1. ሁለት ጊዜ-ይጫኑ ሊነክስ ሚንትን ለ መግጠም
 2. የ እርስዎን ቋንቋ ይምረጡ
_images/installer-language.png
 1. ከ ኢንተርኔት ጋር ይገናኙ
_images/installer-internet.png
 1. እርስዎ ከ ኢንተርኔታ ጋር የ ተገናኙ ከሆነ በ ሳጥኑ ውስጥ ምልክት ያድርጉ የ በርካታ መገናኛ ኮዶች እንዲገጠም
_images/installer-codecs.png
 1. የ መግጠሚያ አይነት ይምረጡ
_images/installer-install.png

እርስዎ በዚህ ኮምፒዩተር ላይ የ ሊነክስ ሚንትን መስሪያ ስርአት ብቻ መግጠም እና መጠቀም ከ ፈለጉ ሁሉንም ዳታ ያጥፉ ከ ሀርድ ድራይቩ ላይ: እና ይምረጡ ዲስክ ማጥፊያ እና ሊነክስ ሚንትን መግጠሚያ

Warning

አዲስ የ ሊነክስ ሚንት መግጠሚያ መመስጠሪያ ለ ደህንነት ሲባል ይህ የሚያሳየው የ ዲስክ መመስጠሪያ ነው: በዚህ ሁኔታ ውስጥ መግጠሚያው የ እርስዎን የ ፊደል ገበታ እቅድ ገና አልተመረጠም ስለዚህ የ ተሰናዳው ለ en_US ነው: እርስዎ ይህን ምርጫ ለ መጠቀም ከ ፈለጉ: የ መግቢያ ቃል ሲያስገቡ ይህን ያስታውሱ: ማስታወሻ: በዚህ ምርጫ አንዳንድ ችግር አለ ለ NVIDIA drivers. እርስዎ አዲስ ተጠቃሚ ከሆኑ የ ቤት ዳይሬክቶሪ መመስጠሪያ ይጠቀሙ: (እርስዎ በኋላ በ መግጠሚያ ውስጥ መምረጥ ይችላሉ)

በ ኮምፒዩተሩ ላይ ሌላ ተጨማሪ የ መስሪያ ስርአት ከ ነበረ: መግጠሚያው ምርጫ ያሳያል ሊነክስ ሚንት ከ ሌላው መስሪያ ስርአት ጎን ለ ጎን እንዲገጠም: እርስዎ ይህን ከ መረጡ መግጠሚያው ራሱ በራሱ የ ነበረውን የ መስሪያ ስርአት እንደገና ይመጥነዋል: እና አጠገቡ ጎን ለ ጎን ሊነክስ ሚንትን ይገጥማል: እርስዎ ኮምፒዩተሩን በሚያስጀምሩ ጊዜ የሚፈልጉትን እንዲመርጡ የ ማስነሻ ዝርዝር ይፈጠራል:

Note

እርስዎ ክፍልፋይ ማስተዳደር ከፈለጉ ወይንም የ ተወሰነ ክፍልፋይ መጠቀም ከ ፈለጉ: ይምረጡ ሌላ ነገር

_images/installer-partitions.png

ሊነክስ ሚንት አንድ ክፍልፋይ ይፈልጋል እንዲጫን በ root / directory.

የ ሊነክስ ሚንት የ መስሪያ ስርአት (ያለ ተጨማሪ ሶፍትዌር ወይንም የ ግል ዳታ) በ ግምት የሚወስደው 15ጌባ ነው: ስለዚህ ለ ክፍልፋዩ ትንሽ ቦታ ይስጡ (100ጌባ ወይንም ከዚያ በላይ)

ext4 እንመክራለን: በጣም የ ተወደደ የ ሊነክስ የ ፋይል ስርአት ነው

_images/installer-partition.png

እንዲሁም ይፍጠሩ የ swap ክፍልፋይ: ይህ ክፍልፋይ የሚጠቅመው ለ hibernation እና አስተማማኝ መሰብሰቢያ ነው: በ ድንገት የ እርስዎ ኮምፒዩተር የ RAM እጥረት ቢገጥመው: ይህን ክፍልፋይ ከ እርስዎ ኮምፒዩተር RAM ጋር እኩል ያድርጉት

 1. የ እርስዎን የ ሰአት ክልል ይምረጡ
_images/installer-timezone.png
 1. የ እርስዎን የ ፊደል ገበታ እቅድ ይምረጡ
_images/installer-keyboard.png
 1. የ ተጠቃሚ ዝርዝር ያስገቡ
_images/installer-user.png

የ እርስዎ ስም ትክክለኛው መሆን ይችላል: ነገር ግን ግዴታ አይደለም: የምንጠቀምበት ለ መመልከቻ ማዳኛ እና ለ መግቢያ መመልከቻ መስኮት ነው

የ እርስዎ ተጠቃሚ ስም የሚገቡበት ስም ይሆናል: እና የ እርስዎ ጋባዥ ስም በ ኔትዎርክ ውስጥ የ ኮምፒዩተሩ ስም ይሆናል

እርስው ችግር ለ ማስወገድ የ ዝቅተኛ ጉዳይ ፊደሎች ባህሪ ይጠቀሙ: ያለ ምንም ስርአተ ነጥብ እና ምልክት

የ እርስዎን የ ግል ዳታ ከ ጥቃት ለ መጠበቅ (አካባቢዎ ካሉ ሰዎች: ወይንም የ እርስዎ ኮምፒዩተር ቢሰረቅ): ምልክት ያድርጉ የ እኔን የ ቤት ፎልደር መመስጠሪያ ላይ

ጠንካራ የ መግቢያ ቃል ይምረጡ

 1. በ እርስዎ ኮምፒዩተር ላይ ሊነክስ ሚንት እስከሚገጠም በ ተንሸራታች ትርኢት ይደሰቱ
_images/installer-slideshow.png

መግጠሙን በሚጨርስ ጊዜ: ይጫኑ አሁን እንደገና ማስጀመሪያ

_images/installer-finished.png

ኮምፒዩተሩ ማጥፋት ይጀምራል እና እርስዎን ይጠይቃል እንዲያስወግዱ የ USB stick (ወይንም ዲቪዲ ): እንደገና በሚጀምር ጊዜ: የ እርስዎ ኮምፒዩተር የ ማስጀመሪያ ዝርዝር ያሳይዎታል ወይንም የ እርስዎን መስሪያ ስርአት ሊነክስ ሚንትን ይጀምራል