ይምረጡ ትክክለኛውን እትም

እርስዎ ማውረድ ይችላሊ ሊነክስ ሚንትን ከ Linux Mint website.

ያንብቡ ከ ታች በኩል ያለውን ለ መምረጥ የትኛው እትም ለ እርስዎ እንደሚስማማ

ሲናሞን: ሜት: ወይንም Xfce?

ሊነክስ ሚንት የሚመጣው በ 3 አይነቶች ነው: እያንዳንዱ የ ተለያየ የ ዴስክቶፕ ገጽታ አላቸው

ሲናሞን ዘመናዊ: እና ሙሉ-የ ዴስክቶፕ ገጽታ አለው
ሜት በጣም አስተማማኝ እና ፈጣን ዴስክቶፕ
Xfce በጣም ቀላል እና አስተማማኝ

በጣም የ ተወደደው የ ሊነክስ ሚንት የ ሲናሞን እትም ነው: ሲናሞን የ ተዘጋጀው በ ሊነክስ ሚንት ነው: በጣም ቆንጆ እና ዘመናዊ ነው

_images/cinnamon.png

ሲናሞን

ሊነክስ ሚንት እንዲሁም ከ ሜት አበልፃጊዎች ጋር ይሳተፋል: የ ኖም 2 ዘመናዊ ዴስክቶፕ ቅጥያ በሆነው: ይህ የ ሊነክስ ሚንት ነባር ዴስክቶፕ ነበር በ 2006 እና 2011 መካከል: ሜት በጣም ፈጣን ነው: የሚጠቀመው አነስተኛ ምንጭ በጣም የ ተረጋጋ ነው ከ ሲናሞን ይልቅ

_images/mate.png

ሜት

Xfce ቀለል ያለ የ ዴስክቶፕ አይነት ነው: በርካታ ገጽታዎችን እንደ ሲናሞን ወይንም ሜት አይደግፍም: ነገር ግን በጣም አስተማማኝ እና በ ምንጮች አጠቃቀም ቀለል ያለ ነው

_images/xfce.png

Xfce

ሶስቱም የ ዴስክቶፕ አይነቶች በጣም ጥሩ ናቸው: እና ሊነክስ ሚንት በ ሶስቱም ይኮራል: አንዳንዶቹ የ ተሻለ ድጋፍ እና ገጽታ አላቸው ከ ሌሎቹ: አንዳንዶቹ ፈጣን ናቸው ከ ሌሎቹ: ሶስቱም በጣም ጥሩ ናቸው: ተጠቃሚው የሚስማማውን መምረጥ ይችላል:

ከ ገጽታ እና አፈጻጸማቸው በስተቀር: ሲናሞን: ሜት: እና Xfce የሚወክሉት ሶስት አይነት የ ተለያየ የ ዴስክቶፕ አቀራረብ ነው: ከ ተለያየ ዝርዝር ጋር እና የ ተለያየ ክፍሎች እና አቀራረብ ማሰናጃ መሳሪያዎች ጋር: እርስዎ የሚወዱትን መርጠው መጠቀም ይችላሉ

እርስዎ እርግጠኛ ካልሆኑ የትኛውን አይነት ዴስክቶፕ እንደሚመርጡ በ ሲናሞን ይጀምሩ: እና ሌሎቹንም ይሞክሩ: ሶስቱም የራሳቸው የሆኑ ደጋፊዎች አላቸው በ ሊነክስ ሚንት ሕብረተሰብ እና ሁሉም የ ተወደዱ ናቸው

32-ቢት ወይንም 64-ቢት?

64-ቢት እንመክራለን

የ 32-ቢት ISO ምስል የሚቀርበው ለ አሮጌ ኮምፒዩተሮች እንዲስማማ ተደርጎ ነው: የ 32-ቢት የሚያስኬዱ ኮምፒዩተሮች በጣም ጥቂት ናቸው: በርካታ ኮምፒዩተሮች ይህን የ 64-ቢት ማስኬድ ይችላሉ: የ እርስዎ ኮምፒዩተር የ ተሰራው ከ 2007 በኋላ ከሆነ: የ እርስዎ ኮምፒዩተር 64-ቢት ማስኬድ ይችላል

እርስዎ አሮጌ ኮምፒዩተር ካለዎት እና እርግጠኛ ካልሆኑ ማስኬድ መቻሉን የ 64-ቢት: ይህን ያንብቡ X86 Chronology.

Tip

እርስዎ መሞከር ይችላሉ ሊነክስ ሚንት 64-ቢት በ እርስዎ ኮምፒዩተር ላይ: ተስማሚ ካልሆነ ምንም መጥፎ ነገር አይፈጠርም: ለ እርስዎ የ ስህተት መልእክት ይታያል