EFI

አስተማማኝ ማስነሻ

እርስዎ ሊነክስ ሚንትን ከ ገጠሙ በኋላ በ EFI ዘዴ: እና እርስዎ ማስነሳት ካልቻሉ በ አስተማማኝ ማስነሻ ስምምነት መጣስ ምክንያት: እርስዎ ከ እነዚህ አንዱን መፍትሄ መሞከር ይችላሉ:

_images/secureboot-violation.jpg
  • መግጠሚያውን እንደገና ማስጀመሪያ:
    • ከ መግጠምዎት በፊት ከ ኢንተርኔት ጋር ይገናኙ

    • እርስዎ አይምረጡ መግጠሚያ ሶስተኛ-አካል ሶፍትዌር graphics እና Wi-Fi hardware, Flash, MP3 እና ሌሎች media.

  • ያሰናክሉ SecureBootBIOS ማሰናጃ ውስጥ በ እርስዎ ኮምፒዩተር ላይ

Note

ለምሳሌ: የ አስተማማኝ ማስነሻ ለ ማሰናከል: ይህን ያንብቡ Managing EFI Boot Loaders for Linux: የ አስተማማኝ ማስነሻ ማስተዳደር.

EFI የ ማስነሻ ቅደም ተከተል

እርስዎ ሊነክስ ሚንትን በ EFI ዘዴ ከ ገጠሙ በኋላ: እና የ እርስዎ ኮምፒዩተር የ ማስነሻ ዝርዝሩን ከ ዘለለ እና በ ቀጥታ ወደ ሌላ Windows (ወይንም ሌላ የ መስሪያ ስርአት) ካስነሳ: የ እርስዎ ማስነሻ ቅደም ተከተል ችግር አለው ማለት ነው

የ ማስነሻ ቅደም ተከተል ለ መቀየር:

  1. ሊነክስ ሚንት ማስነሻ በ live ዘዴ (በ እርስዎ USB stick ወይንም ዲቪዲ).

  2. ተርሚናል ይክፈቱ

  3. Type sudo efibootmgr and press Enter.

ይህ ትእዛዝ ዝግጁ የሆኑ የ ማስነሻ ምርጫ እና የ ማስነሻ ደረጃ ዝርዝር ያሳያል

_images/efibootmgr.png

በ መመልከቻው ፎቶ ከ ላይ በኩል ሶስት አይነት የ ማስነሻ ምርጫዎች አሉ:

  • ubuntu at 0000

  • linuxmint at 0001

  • Mac OS X at 0081

ይህ የ ማስነሻ ደረጃ 0081: ይህ የሚያሳየው ኮምፒዩተሩ ለ ማስነሳት የሚሞክረው የ Mac OS ነው እና ሊነክሥ ሚንትን አይደለም

Important

በ ቴክኒካል ምክንያት ሊነክስ ሚንት የሚጠቀመው ኡቡንቱ ነው እንደ EFI ማስነሻ ስም

  1. የ ማስነሻ ቅደም ተከተል ለ ማስተካከል: ይጻፉ: sudo efibootmgr --bootorder XXXX,YYYY (ይህ XXXX እና YYYY የ መስሪያ ስርአት ማስነሻ ምርጫ ናቸው እርስዎ ማስነሳት የሚፈልጉት)

_images/efibootmgr-2.png

ከ ላይ የሚገኘው የ መመልከቻ ፎቶ sudo efibootmgr --bootorder 0000,0081 ለ ኮምፒዩተሩ ትእዛዝ ይሰጠዋል ሊነክስ ሚንት መጀመሪያ እንዲነሳ (ubuntu ይሆናል የ EFI ማስነሻ ስም ለ ሊነክስ ሚንት) እና ከዛ Mac OS.

  1. ኮምፒዩተሩን እንደገና ያስጀምሩ

Note

ከ ላይ የሚታየው የ መመልከቻ ፎቶ``0000`` የ መጀመሪያው የ ማስነሻ ምርጫ ነው ስለዚህ ኮምፒዩተሩ የሚነሳው በ ሊነክስ ሚንት grub menu ነው: ይህ grub ካልተሳካ (ወይንም ከ ተወገደ በ መውጫ ትእዛዝ: ) ኮምፒዩተሩ የሚከተለው የ ማስነሻ ቅደም ተከተሉን ነው: እና ይህን ለ ማስነሳት ይሞክራል 0081: ይህ የሚያመለክተው ወደ Mac OS ነው: